የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት በህግ ተደንግጎ የተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች
ማለትም ህግ የማውጣት፣ አሰፈጻሚ አካላትን የመቆጣጠር እንዲሁም ሌሎች የህዝብ ጥቅም የሚያስከብሩ የዉክልና ተግባራትን ማከናወን ነው፡፡
ርዕይ
በ2023 በህግ አወጣጥ፣ክትትል ቁጥጥር እና ውክልናን በመወጣት በቴክኖሎጂ የታገዘና ተጠያቂነትን ያሰፈነ የህዝብ ተሳታፊና ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ም/ቤት ሆኖ ማየት
ተልዕኮ
የህዝብ ፍላጎትና ጥቅምን ያስቀደመ ሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመሠረተ ጥራት ያለው ህግ በማውጣት፣ጠንካራ የክትትል ቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ፣መልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነትን ማጠናከር፣
እሴቶች
ክብር ለታላላቆች ለአገራችን ምሰሶዎች ነው እና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣረስ ህግ እንዳልወጣ ይቆጠራል፡፡
“እረኛ ከበጎቹ ተነጥሎ አይታይም” እንዲሉ አንድ ተወካይ ሀሳብ የብዙ ህዝብ ድምፅ ነው፡፡
የተደበቀ መጋለጡ ፣የተገለጠ መታመኑ አይቀርም እና ስራዎቻችን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን፡፡
የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ፤እንዲሉ ለመረጠን ህዝብ ፍላጎት እና ለእውነት እንታመናለን
ከልጅ ልጅ ቢለዩ አመትም አይቆዩ ነው እና ሁሉንም ህዝብ በፍትሃዊነት እናገለግላለን
አንድ እጅ አያጨበጭም ፣አንድ በሬ አያስብም እንዲሉ የህዝብ ተሳትፎን በሁሉም ተግባራት እናረጋግጣለን
የአበባ ውበቱ የቀለም ልዩነቱ እንዲሉ ልዩነታችን ውበታችን ነው፡፡
ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው እና ለትብብር ቅድሚያ እንሰጣለን
ሎሚ ካልመጠጡት እምቦይ፣ዳቦ ካልገመጡት ድንጋይ እንዲሉ ብቃት እና ውጤታማነትን እንመዝናለን፡፡
